ኢባትሎ 108 ነጥብ 78 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ (ኢባትሎ) በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት 108 ነጥብ 78 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘሁ አለ፡፡
ኢባትሎ በዛሬው ዕለት የሰራተኞች ቀን ሲያከብር ዋና ስራ አስፈፃሚው በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ በጭነት አስተላላፊነት፣ በወደብ ተርሚናል እና በኮርፖሬት አገልሎት ዘርፎች ውጤት ተመዝግቧል፡፡
በበጀት ዓመቱ 101 ነጥብ 86 ቢሊየን ብር ለማግኘት ታቅዶ 108 ነጥብ 78 ቢሊየን ብር ገቢ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል።
የኢባትሎ ቦርድ ሰብሳቢ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ፤ ተቋሙ ውጤታማ ስራዎችን በማከናወን ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል ነው ያሉት።
በተቋሙ የሰራተኞች ቀን መርሐ ግብሩ ላይ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች ተገኝተዋል።
የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አመራሮችና ሰራተኞች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል።
በየሻምበል ምህረት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!