ሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ተመርጠዋል፡፡
የ2017 የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (የመጅሊስ) ምርጫ በዛሬው ዕለት ተጠናቅቋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምስረታ እና የሥራ አስፈጻሚዎች ምርጫ መካሄዱም ተመላክቷል፡፡
በዚህ መሰረትም ሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት በመሆን በድጋሚ ተመርጠዋል፡፡
ሼህ አብዱልከሪም በድረድ ደግሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ተቀዳሚ ም/ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸው ተገልጿል፡፡
ሼህ ጁኔይድ ሀምዛ እና ሼህ ሀሚድ ሙሳ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ም/ፕሬዚዳንት በመሆን የተመረጡ ሲሆን÷ ኡስታዝ ተምኪን አብዱላሂ ደግሞ ዋና ፀሃፊ ሆነው ተመርጠዋል።
የተመረጡ የሥራ አስፈጻሚ አባላት በታላቁ አንዋር መስጅድ ቃለመሃላ መፈጸማቸው ተጠቁሟል፡፡
በጀማል አህመድ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!