Fana: At a Speed of Life!

የታንዛኒያ ም/ፕሬዚዳንት ፍሊፕ ኢዝዶሪ ምፓንጎ (ዶ/ር) አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተለያዩ ሀገራት መሪዎች በ2ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ እየገቡ ነው፡፡
በዚህ መሰረትም የታንዛኒያ ም/ፕሬዚዳንት ፍሊፕ ኢዝዶሪ ምፓንጎ (ዶ/ር) እና የሊቢያ የፕሬዚዳንሻል ም/ቤት ም/ፕሬዚዳንት ሙሳ ኢልኮን ዛሬ ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ገብተዋል።
መሪዎቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የፍትሕ ሚኒስትር ሐና አርአያስላሴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
2ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ “ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መፍትሄዎችን ማፋጠን፣ የአፍሪካን አረንጓዴ ልማት በፋይናንስ መደገፍ” በሚል መሪ ሃሳብ ይካሄዳል፡፡
አፍሪካ እየገጠሟት ያሉ አንገብጋቢ ፈተናዎችን በዘላቂነት መሻገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚመክረው ጉባዔ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግ
ኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.