የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የ2017 ጠቅላላ ምርጫ በሕዝበ ሙስሊሙ የነቃ ተሳትፎ ተጠናቅቋል – ሰላም ሚኒስቴር
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 ጠቅላላ ምርጫ በሰላምና በሕዝበ ሙስሊሙ የነቃ ተሳትፎ በመጠናቀቁ ሰላም ሚኒስቴር ለዕምነቱ ተከታዮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
ሚኒስቴሩ በእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱ ÷ ሕዝበ ሙስሊሙ መሪውን በድምፁ በመምረጥ ተቋሙን በነፃነት ለመምራት ለዘመናት ሲታገል መቆየቱን አስታውሷል።
ለውጡን ተከትሎ በተፈጠረው መልካም ዕድልም ጠቅላይ ምክር ቤቱ በአዋጅ ሊቋቋም ችሏል ነው ያለው፡፡
ሕዝበ ሙስሊሙ በነፃነት ለቀጣይ 5 ዓመታት ተቋሙን የሚመሩ መሪዎችን በነቃ ተሳትፎ፣ በብልኅነት፣ በከፍተኛ ሀገራዊ ስሜትና ኃላፊነት መምረጡን አንስቷል፡፡
ምርጫው አካታችና የመላውን ሕዝብ ሰላምና ሀገራዊ የአብሮነት መንፈስን በሚያጠናክር መልኩ በመጠናቀቁም ሚኒስቴሩ የተሰማውን ደስታ ገልጿል።
ሚኒስቴሩ በየደረጃው ተቋሙን ለመምራት ኃላፊነትን ከተረከቡት የዕምነቱ አባቶች ጋር በቅርበት እንደሚሰራ አረጋግጧል፡፡
ጠቅላይ ምክር ቤቱ በሰላም፣ በማኅበራዊ ልማት እና በሀገር ግንባታ ዙሪያ የጀመረውን በጎ ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያለውን ተስፋም ገልጿል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!