Fana: At a Speed of Life!

ከለውጡ በኋላ የኢትዮጵያን ሕብራዊ ገፅታ ለመግለፅ የተደረጉ ጥረቶች ፍሬያማ ናቸው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እንደ ሀገር ከጀመርነው የለውጥ ጉዞ በኋላ የኢትዮጵያን ሕብራዊ ገፅታ ለመግለፅ ያደረግናቸው ጥረቶች ፍሬያማ ነበሩ አሉ በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፡፡
አቶ አደም ፋራህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ÷ዛሬ ጷጉሜን 2 የኅብር ቀንን በሀገር አቀፍ ደረጃ ስናስብ ውለናል ብለዋል።
በተለይም እንደ ሀገር ከጀመርነው የለውጥ ጉዞ በኋላ የኢትዮጵያን ሕብራዊ ገፅታ ለመግለፅ ያደረግናቸው ጥረቶች ፍሬያማ ነበሩ ነው ያሉት።
በውጤቱም በኅብር የደመቀች ሕብራዊት ኢትዮጵያን ለመፍጠር የብዙ ብሔሮች፣ ቋንቋዎች፣ ባህሎች፣ እምነቶች፣ ሥልጣኔዎችና የብዙ ጀግኖች ሀገርነቷን ለማስቀጠል ችለናል ሲሉ ተናግረዋል።
አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመገንባት በተጓዝንባቸው ርቀቶች ሁሉ ኅብረ ብሔራዊነታችን መልካችን፣ አንድነታችን ሕልውናችን መሆኑን አሳይተናል ብለዋል፡፡
እንዲሁም የተበታተንን ኅብሮች እንጂ የተጨፈለቅን አንድ ዓይነቶች እንዳልሆንን ለዓለም አሳይተናል ነው ያሉት።
እኛ ኢትዮጵያውያን ላንበጠስ የተጋመድን ክሮች፣ በብዙ ቀለማት የተሰበዝን ህብሮች፣ በወንድማማች እህትማማቻዊ ሕብረ ብሄራዊነት አንድነታችን የፀና እቶኖች፣ ላንለያይ የተሰፋን የመሰናሰል ምሳሌዎች ነን ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.