Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ግሬናዳ ትብብራቸውን ለማጠናከር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከግሬናዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆሴፍ አንድል ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በአፍሪካና ካሪቢያን ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ትስስር ወደ ተጨባጭ ትብብር መቀየር እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
ኢትዮጵያና ግሬናዳ በቀጣይ በጤና፣ በዲፕሎማሲ፣ በሠለጠነ የሰው ሃይል ስምሪት እና በአቪዬሽን ዘርፍ በትብብር በሚሰሩበት ሁኔታ ላይም መክረዋል፡፡
ሚኒስትሮቹ ከ2ኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ሀገራት መሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን ነው የተወያዩት፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.