Fana: At a Speed of Life!

ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጡ እመርታዎችን አስመዝግበናል – አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ መሰረት የጣሉ አስደናቂ እመርታዎችን አስመዝግበናል አሉ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ የእመርታ ቀንን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት÷ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሀገር በቀል እሳቤዎች ሀገራዊ አቅሞችን መጠቀም ያስቻሉ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡
ለአብነትም የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች እና በርካታ የልማት ኢኒሼቲቮችን መተግበር ተችሏል ነው ያሉት፡፡
የተረጂነትና የጠባቂነት አስተሳሰብን በመስበር አይቻልም በተባሉ መስኮች ጭምር ምርታማነትን በማሳደግ ቀጣይነት ያለው ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መመዝገቡንም ጠቅሰዋል፡፡
በሁሉም የኢኮኖሚ እድገት ዘርፎች እና የዘላቂ ልማት ግቦች ተጨባጭ እመርታዊ ለውጥ ማሳካት መቻሉን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ይህም በየወቅቱ የሚገጠሙ ፈተናዎችን በመተባበርና በጽናት በመሻገር ብልጽግናችንን በተሟላ ሁኔታ ማረጋገጥ እንደምንችል ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.