Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል ህዝቡ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅበታል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2017 (ኤፍ ኤምሲ) የኢትዮጵያን የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል ህዝቡ በተሰማራበት የስራ ዘርፍ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅበታል አሉ የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር)፡፡
የእመርታ ቀን “እመርታ ለዘላቂ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በጋምቤላ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ እስካሁን ያሳካናቸውን ድሎችና አጠቃላይ እመርታዎች በአግባቡ ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ይገባል።
በክልሉ የተመዘገቡ እመርታዎችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው፥ የክልሉ ሰላም በዘላቂነት እንዲቀጥል በመከባበርና አንድነታችንን በማጎልበት ለፈጣን እመርታ መትጋት አለብን ነው ያሉት።
የክልሉ ውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኡጁሉ ኡዶል በበኩላቸው፥ የእመርታ ቀንን የምናከብረው እንደ ክልል ባለፉት 7 አመታት ያስመዘገብናቸውን ስኬቶቻችንን በማፅናት ያልተሻገርናቸው ሳንካዎች በመለየት ነው ብለዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.