Fana: At a Speed of Life!

ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት አዲስ ብስራት ይዘን መጥተናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የነዋሪዎቻችንን እንግልት የሚቀንስ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት በአዲሱ አመት አዲስ ብስራት ይዘን መጥተናል አሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር (ዶ/ር) ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ስራ አስጀምረዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ ለከተማችን ነዋሪዎች በአዲሱ አመት ዋዜማ የተበረከተ ገጸ በረከት ነው ብለዋል፡፡

በ13 ተቋማት 107 አገልግሎቶችን የሚሰጠው አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል የነዋሪዎችን እንግልት የሚቀንስ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት ለማቅረብ ያስችላል ነው ያሉት፡፡

ከንቲባዋ በአዲሱ አመት በብዙ ብርታትና ትጋት ለማገልገል ዝግጁ ነን ማለታቸውን የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.