ኤለን መስክ የዓለም ቁጥር አንድ ቱጃርነት ስፍራውን አስረከበ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም ቁጥር አንድ ቱጃር የነበረው አሜሪካዊው ቢሊየነር ኤለን መስክ የቀዳሚነት ስፍራውን በኦራክል ኩባንያ መስራች ላሪ ኤሊሰን አስረክቧል።
አጠቃላይ 385 ቢሊየን ዶላር ሀብት የነበረው ኤለን መስክ እስከ ትናንትና ድረስ 101 ቢሊየን ዶላር ሃብት በነበረው ላሪ ኤሊሰን በስምንት ቢሊየን ዶላር ተበልጦ የዓለም ቁጥር ሁለት ቱጃር ሆኗል።
ላሪ ኤሊሰን ትናንትናው ባወጣው የገቢ ሪፖርት አጠቃላይ ሀብቱ ወደ 393 ቢሊየን ዶላር ከፍ በማለቱ የዓለም ቁጥር አንድ ቱጃር ለመባል በቅቷል።
የዳታ አስተዳደር ኩባንያ ባለቤቱ አሊሰን በዚህ ፍጥነት ተምዘግዝጎ የዓለም ቁጥር አንድ ቱጃር መሆኑ ብዙዎችን ማስገረሙን ብሉምበርግ ዘግቧል።
የኩባንያው የአክሲዮን ዋጋ ዛሬ ማለዳ ላይ በ40 በመቶ ከፍ ማለቱም ተነግሯል።
በአቤል ነዋይ