Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የባህል ዲፕሎማሲን ለማጠናከር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ ናት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የባህል ዲፕሎማሲን ለማጠናከር ከሁሉም ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ ናት አሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማህዲ።

የ60 ሀገራት የባህልና ኪነ ጥበባት ዘርፍ ሚኒስትሮች እና ተወካዮች የሚሳተፉበት፤ 11ኛው ኢንተርናሽናል ዩናይትድ ከልቸር ፎረም ላይ ኢትዮጵያ እየተሳተፈች ትገኛለች።

በፎረሙ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማህዲ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ቀደምት የስልጣኔ፣ የአስደናቂ ቅርሶች፣ የብዝሃ ባህል፣ ማንነትና ቋንቋ ባለቤት ናት።

የሰው ልጆች እንዲሁም 76 ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መገኛ የሆነች ህዝቦቿ የራሳቸው ቋንቋዎች፣ ሙዚቃ፣ ጥበባት ያሏት ብዝሃነቷ ጥንካሬ የሆናት ሀገር ናት ብለዋል።

ፎረሙ በባህል፣ ጥበባትና ፈጠራ ኢንደስትሪ የጋራ የሆነ መረዳትና ትብብር እንዲኖር እንደሚያደርግ መሆኑን በማንሳት ኢትዮጵያ ለመሰል መድረኮች ትኩረት እንደምትሰጥ ጠቁመዋል።

አክለውም ባህል ህዝቦችን ለማስተሳሳርና ለማገናኘት እንደ ድልድይ የምንጠቀመው ለሀገራት ዲፕሎማሲ እና ሰላም መንገድ የሚከፍት መሆኑን አመልክተዋል።

“Return to Culture – New Opportunities.” በሚል መሪ ኃሳብ የሚካሄደው ፎረሙ የባህል ንግድ፣ ሲኒማ፣ ቅርሶች፣ ሙዚቃ፣ ቴአትር፣ ሰርከስ፣ የጥበባት ትምህርትን ጨምሮ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ይመክራል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.