አየር መንገዱ የፓን አፍሪካ መገለጫ የሆነ አኅጉራዊ ተቋም ነው – አቶ መስፍን ጣሰው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ እውነተኛ የፓን አፍሪካ መገለጫ የሆነ አኅጉራዊ የአቪየሽን ተቋም ነው አሉ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው።
አየር መንገዱ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት፣ አጋር አካላትና ዲፕሎማቶች በተገኙበት በቢሾፍቱ አቅራቢያ ስለሚገነባው ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ እና የአየር መንገዱን ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ብሎም ቀጣይ ርዕዮችን አቅርቧል።
አቶ መስፍን ጣሰው በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአኅጉሪቱ ቀዳሚው የአቪየሽን ተቋምነቱን አጠናክሮ አስቀጥሏል።
አየር መንገዱ ደህንነት እና የአገልግሎት ምቹነት ከቀዳሚ ግቦቹ መካከል እንደሆነ እና አፍሪካን ከተቀረው ዓለም እያስተሳሰረ ለደንበኞቹ አስተማማኝ አገልግሎት መስጠቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የደንበኞች ቁጥር በፍጥነት አያደገ መምጣቱን እና ላለፉት 3 ዓመታት የቢሾፍቱ አቡሴራ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ለማስጀመር ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት የዝግጆት ስራዎች ሲከናወን መቆየቱን ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ መንግስትም ለፕሮጀክቱ ያልተቋረጠ ድጋፍ ማድረጉን አውስተው፥ ለዚህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አማካኝነት የፕሮጀክቱን ሂደት የሚከታተል ብሔራዊ ዐቢይ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል።
አዲሱ የአቡሴራ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ፕሮጀክት አፍሪካን እርስ በርስ እና ከተቀረው ዓለም ለማስተሳሰር ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጸው÷ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እውነተኛ የፓን አፍሪካ መገለጫ የሆነ አፍሪካዊ የአቪየሽን ተቋም እንደሆነም ተናግረዋል።
የአፍሪካ ልማት ባንክ ተወካይ በበኩላቸው÷ በአኅጉሪቱ የአቪየሽን ታሪክ ትልቁ ነው የተባለለትን ፕሮጀክት የፋይናንስ ማመቻቸት ተግባሩን እንዲያከናውን መመረጡን በማንሳት ባንኩ ከአጋር አካላት ጋር በመሆን ለፕሮጀክቱ ስኬት በቁርጠኝነት መሥራቱን ይቀጥላል ብለዋል።
በፕሮጀክቱ ላይ መዋዕለ ንዋይ ፈሰስ ማድረግ ፓን አፍሪካኒዝምን ከፍ ከማድረጉ ባሻገር አኅጉራዊ ትስስርን እና የአፍሪካን የአቪየሽን ዘርፍ እድገት ግስጋሴውን ያፋጥናል ሲሉ በመድረኩ ለተሳተፉት ዓለም አቀፍ ባድርሻ እና አጋር አካላት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
አዲሱ የቢሾፍቱ አቡሴራ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ግንባታ ጥቅል ወጭ እስስከ 10 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ እንደሆነ እና ባንኩ ከተሰጠው የፋይናንስ ፍሰት ማስተባበር ባለፈ የራሱን 500 ሚሊየን ዶላር ማመቻቸቱን አስታውሰዋል።
በመሳፍንት ብርሌ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!