የቱሪስት አገልግሎት ጥራት እንዲኖረው ለማድረግ ያለመ ንቅናቄ ሊጀመር ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሪስት አገልግሎት ጥራት እንዲኖረው ለማድረግ ያለመ ንቅናቄ “የአገልግሎት ልህቀት ከእኔ ይጀምራል” በሚል መሪ ሐሳብ ሊጀመር ነው።
የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ንቅናቄው የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን የሚያሳትፍ መሆኑን ገልጸው÷ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪዎች የሚሰጡት አገልግሎት ጥራት እንዲኖረው ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪዎች በሚሰጡት የአገልግሎት ልህቀት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አንስተዋል።
ክልሎችን ጨምሮ በቱሪዝም መዳረሻዎች አካባቢ ያሉ የመንግስት መዋቅሮች ንቅናቄውን ተቀላቅለው አገልግሎት ለሚሰጡ አካላት ግንዛቤ የማሳደግ ሥራ በጋራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል በበቂ መጠን አለመገኘት ችግር መሆኑን አንስተው÷ ይህን ለመቅረፍ እንዲቻል የቱሪስት ማሰልጠኛ ተቋማት ጋርም በጋራ ይሰራል ነው ያሉት።
አስጎብኚዊች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የቱሪስት መዳረሻዎችና ሌሎችም የቱሪዝም ቤተሰቦች በንቅናቄው እንደሚሳተፉ ተናግረዋል።
በፌቨን ቢሻው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!