Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል የመስቀል ደመራ በዓልን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ተጠናቅቋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል የመስቀል ደመራ በዓልን በድምቀት ለማክበር አስፈለጊው ዝግጅት ተጠናቅቋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የጋምቤላና የደቡብ ሱዳን አኅጉረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መጋቤ ሥርዓት ዴንግ ሬስ በዓለም በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበውን የመስቀል ደመራ በዓል የሕዝቡን አብሮነት በሚያጠናክር መልኩ ለማክበር ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

በዓሉ ከሃይማኖታዊ ትውፊቱ ባለፈ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪው ልማት ያለውን አስተዋጽኦ ታሳቢ በማድረግ በድምቀት ለማክበር እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዓሉን ለማድመቅ ክብረ በዓሉ የሚከበርባቸውን ሥፍራዎች የማስዋብ ስራ መከናወኑን አስረድተዋል።

የክልሉ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ ፔል ፒተር በበኩላቸው÷ መስቀል ደመራ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች የሚታደሙበት በዓል በመሆኑ ወደ ክልሉ የሚመጡ እንግዶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ አስፈላጊው ዝግጅት እንደተደረገ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.