በሶማሌ ክልል የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን ለማሳለጥ…
አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ይበልጥ ለማሳለጥ በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ፡፡
የቢሮው ኃላፊ አሕመድ ረሺድ እንዳሉት÷ በክልሉ በአምራች ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ልማት ላይ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ናቸው።
ለአብነትም ባለፉት ሰባት ዓመታት 44 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 4 ሺህ 571 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን ተናግረዋል።
በኢንዱስትሪ፣ ግብርና፣ ቤት ልማት፣ ትራንስፖርት፣ ሆቴል፣ ቢዝነስ ሴንተርና ሌሎች ዘርፎች ፈቃድ መሰጠቱን አስረድተዋል፡፡
እስካሁን 155 ፕሮጀክቶች ምርትና አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ጠቁመው ÷ በክልሉ የኢንዱስትሪ ልማቱን የሚያስፋፉና የሚያሳልጡ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡
በዚህ መሠረትም የኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማሳደግና ምርታማነታቸውን ለማረጋገጥ፣ ለተኪ ምርት እና የግብርና ምርቶች ማቀነባበር ላይ ትኩረት መደረጉን አብራርተዋል።
ከሥራ ዕድል ፈጠራ አኳያ በኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች በድምሩ ለ80 ሺህ ወገኖች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ነው ያሉት፡፡
በክልሉ የተፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎች ዳያስፖራዎች በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ማስቻላቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በተለይም የኢኮኖሚ ሪፎርሞች እና በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያሉ ምቹ ሁኔታዎች ዳያስፖራው በኢንቨስትመንት የሚያደርገውን ተሳትፎ እንዳሳደገው ነው ያስረዱት፡፡
6 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ከ740 የሚልቁ ዳያስፖራዎች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እንደተሰማሩ መናገራቸውን ኢዜአ ነው የዘገበው፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!