Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ግዙፍ የልማት ዕቅዶች ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት…

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክት ዕቅዶች የሀገርን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ ጉልህ ድርሻ ይኖራቸዋል አሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ በ30 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ወጪ የሚገነቡ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክት ዕቅዶችን ማብሰራቸው ይታወሳል።

ሚኒስትር ዴኤታው ሕዳሴ ግድቡ የኢትዮጵያ ብልጽግና ማብሰሪያ የሀገር ማንሰራራት መገለጫ ለመሆን መብቃቱን አንስተዋል።

ኢትዮጵያዊያን ለግድቡ የግንባታ ሂደት በሁሉም መስክ በኅብር ያበረከቱት አስተዋጽኦም የቅድመ አያቶችን የመቻል መንፈስ የገለጠ አኩሪ የልማት ገድል መሆኑን ገልጸዋል።

የሕዳሴ ግድብ የሚያመነጨው የኃይል አቅርቦትም ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ እያስመዘገበች የምትገኘውን የልማት ስኬት ለማሳለጥ ወርቃማ ዕድል ይዞ መምጣቱን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያዊያን አደባባይ በመውጣት የግድቡ መጠናቀቅን አስመልክቶ በከፍተኛ የደስታ ስሜት ማክበራቸውን አስታውሰው÷ የግድቡ መጠናቀቅ ተጨማሪ ግዙፍ ብሔራዊ የልማት ዕቅድ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ መነሻ ሆኖ የሚያገለግል መሆኑን አብራርተዋል።

በቀጣይ የሚገነቡ ግዙፍ ፕሮጀክቶችም መሠረተ ልማትን በማሟላት፣ የኃይል አቅርቦትን ለማሳደግ እንዲሁም የግብርና ምርታማነትን ለማላቅ የማይተካ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ተናግረዋል።

መንግስትም የኢትዮጵያን የዕድገትና ብልጽግና ጉዞ በማሳለጥ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፃቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

የሰላማዊ የኒውክሌር ማብላያ፣ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ፋብሪካ፣ የአየር ማረፊያ፣ የማዳበሪያ ፋብሪካና መሰል የልማት ግንባታዎችም የዕድገት ከፍታን ለማፅናት ትርጉም የሚሰጣቸው እንደሆኑ አንስተዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.