የእያንዳንዱ ስኬት ዓላማ የኢትዮጵያን ማንሰራራት ዕውን ማድረግ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የእያንዳንዱ ስኬት ዓላማ ተሰናስሎ የኢትዮጵያን ማንሰራራት ዕውን እንዲሆን ማድረግ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ እና የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ መሰረተ ድንጋይ መቀመጡን ተከትሎ ባስተላለፉት ምልዕክት ነው ይህንን ያሉት።
ዛሬ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አነቃቂ እና ለኢትዮጵያ ብልጽግና ትልቅ መሰረት የሚጥል ስራዎች መጀመሩን ገልጸው÷ ይሄንን ስራ የስኬቶቻችን ማብሰሪያ የማንሰራራታችን ማሰሪያ አድርገን እንወስደዋለን ብለዋል።
የእያንዳንዱ ስኬት ዓላማ ተሰናስሎ የኢትዮጵያን ማንሰራራት ዕውን እንዲሆን ማድረግ በመሆኑ ለመላው ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
2017 እና 2018 ዓ.ም ልክ እንደ 100 ዓመታት የሰፋ ጊዜ ለኢትዮጵያ ማምጣቱን በመግለጽ በእነዚህ ጊዜያት ሕዳሴ የተባለው የንጋት ብስራት የሆነው የተበሰረበት ከፍተኛ የኢነርጂ ፕሮጀክት መመረቁን አስታውሰዋል።
አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ደግሞ ወደ 10 ቢሊየን የሚጠጋ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መጀመራቸውን እና መመረቃቸውን ተናግረዋል።
ዛሬ ለሶማሌ የብልጽግና ጸሐይ ወጣላት ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ÷ ይህ በክልሉ የታየው ብርሃን በመላው ኢትዮጵያ እስኪረጋገጥ እና እያንዳንዱ ዜጎች ካሉበት የድህነት አረንቋ አውጥቶ ወደሚገባቸው የብልጽግናና የልማት ደረጃ እስኪደርሱ ድረስ መትጋት ይጠበቅብናል ብለዋል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!