Fana: At a Speed of Life!

አቶ አደም ፋራህ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

አቶ አደም ፋራህ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ለ2018 የኢሬቻ መልካ ክብረ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

የ2018 የኢሬቻ በዓል “ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል ሆረ ፊንፊኔ በነገው ዕለት እንዲሁም ሆረ ሀርሰዴ ከነገ በስቲያ እሑድ በድምቀት ይከበራል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.