በክልሎች መካከል ፍትሐዊ የድጎማና የጋራ ገቢዎች ክፍፍልን ማረጋገጥ ለፌዴራል ሥርዓት ጽኑ መሠረት ነው – አቶ አሻድሊ ሀሰን
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በክልሎች መካከል ፍትሐዊ የድጎማና የጋራ ገቢዎች ክፍፍልን ማረጋገጥ ለጠንካራ የፌዴራል ሥርዓት ፅኑ መሰረት ነው አሉ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፡፡
ለ6ኛው የፓርላማ ዘመን፣ 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በሚቀርቡ ረቂቅ የውሳኔ ሀሳቦች ላይ የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ውይይት አድርጓል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አቶ አሻድሊ ሀሰን በወቅቱ እንዳሉት÷ ፌዴራላዊ ሥርዓት ከሌሎች ሥርዓተ መንግሥታት በተሻለ ደረጃ የሕዝቦችን በፍትሐዊነት የመበልፀግ ዓላማ ለማሳካት ያስችላል።
ለሥርዓቱ ዘላቂነት ፍትሐዊ የሃብት ክፍፍልንና ውጤታማ የፊስካል ሽግግርን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
በ2017 በጀት ዓመት የበይነ መንግሥታት የፊስካል ሽግግሮችን በፍሐዊነትና በውጤታማነት ለማስፈጸም የሚያስችል ተግባራት መከናወናቸውን አስታውሰዋል።
ለውጡን ተከትሎ በተደረገ ማሻሻያ የክልል መንግሥታት ድርሻ በ2012 በጀት ዓመት ከነበረበት 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በ2017 በጀት ዓመት ወደ 91 ነጥብ 73 ቢሊየን ብር ማደጉን አብራርተዋል፡፡
የድጎማ በጀት ቀመር ለማሻሻል የሚያስችሉ ተግባራት የተያዘው በጀት ዓመት ዋና የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
በተለያዩ ቻናሎች ወደ ክልል የሚደረጉ የፊስካል ሽግግሮችና የፌዴራል የመሠረተ ልማት ስርጭቶች በተዘረጋው አሠራር መሠረት እየተከናወኑ ስለመሆናቸው ማረጋገጥም ትኩረት እንደሚሰጠው ተናግረዋል።
ቋሚ ኮሚቴው በዛሬው ውሎው በ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ እቅድ ላይ መወያየቱንም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ተረፈ በዳዳ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!