Fana: At a Speed of Life!

በተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በማንሰራራት ላይ ይገኛል – ፕሬዚዳንት ታዬ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ተግባራዊ በተደረገው የማክሮ ኦኮኖሚ ማሻሻያ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በማንሰራራት ላይ ይገኛል አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፡፡

6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤትና የፌዴሬሽን ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ሁለቱ ምክር ቤቶች ዓመታዊ ሥራቸውን እንደጀመሩ በማብሰር የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው በ2017 በጀት ዓመት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ የሚያሳድጉ በርካታና መጠነ ሰፊ ሥራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል፡፡

አዲሱ ዓመት የብዙ ዓመት ቁጭታችን የነበረውን ሕዳሴ ግድብ የመረቅንበት፣ የተፈጥሮ ጋዝ ያወጣንበትና ግዙፍ ፕሮጀክቶችን የጀመርንበት በመሆኑ በታሪክ የሚወሳ ነው ብለዋል፡፡

ተግባራዊ በተደረገው የማክሮ ኦኮኖሚ ማሻሻያ መሰረት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በማንሰራራት ላይ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለዘመናት በመዋቅራዊ ተግዳሮቶች ተጽዕኖ ሥር ወድቆ በከፍተኛ የዕዳ ጫና ውስጥ ይገኝ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በለውጡ መንግስትም የኢኮኖሚ መዛባትን የሚያርሙና ወደ ኢኮኖሚ ብልጽግና የሚወስዱ ፈጣንና መጠነ ሰፊ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን አብራርተዋል፡፡

አሁን ላይ መንግስት ኢኮኖሚውን ከዕዳ ጥገኝነት ወደ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት ለማሸጋገር የሚያስችል ወሳኝ ምዕራፍ መክፈቱን ነው ያስገነዘቡት፡፡

የኢኮኖሚ ለውጡ መሰረቶችም ያሉንን አቅሞች ማወቅ፣ በችግር ውስጥ ዕድልን ማየት፣ በፈጠራ እና በፍጥነት ዘላቂ ግቦችን በማሳካት ላይ ያተኮሩ ናቸው ብለዋል፡፡

በዚህም ከዕዳ ጫና በመላቀቅ በራስ አቅም ችግሮችን በመፍታት ከአግላይ የኢኮኖሚ ሥርዓት ወደ አሳታፊ እና ምቹ ምህዳር በመሸጋገር የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጥረት ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.