Fana: At a Speed of Life!

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒ እንዲሆን በሃላፊነት ይሰራል – ፕሬዚዳንት ታዬ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በተያዘው ዓመት የሚካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒ እንዲሆን መንግስት በሃላፊነት ይሰራል አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፡፡

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤትና የፌዴሬሽን ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ሁለቱ ምክር ቤቶች ዓመታዊ ሥራቸውን እንደጀመሩ በማብሰር የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው በተያዘው ዓመት የሚካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን መንግስት በሃላፊነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡

እንዲሁም ሀገራዊ ምርጫው በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተዓማኒ እንዲሆን በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ነው አጽንኦት የሰጡት፡፡

መላው ሕዝብ ኢትዮጵያ ያቀደቻቸውንና የጀመረቻቸውን ግዙፍ የለውጥ እርምጃዎች አበርትቶ እንዲደግፍ እና በትጋት እንዲሳተፍ ፕሬዚዳንቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወዳጆች እና የብልጽግና አጋሮች ከኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ ጎን በመቆም ለተያዘው ስኬት ሁነኛ አጋር እንዲሆኑም ጠይቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ታዬ 2018 በጀት ዓመት የተግባር እና የስኬት ዓመት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.