ለክልሎች የተንቀሳቃሽ ክሊኒክ አምቡላንሶች ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጤና ሚኒስቴር ለዘጠኝ ክልሎች 450 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የተንቀሳቃሽ ክሊኒክ አምቡላንሶች ድጋፍ አድርጓል።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ÷ አምቡላንሶቹ ከጃፓን መንግስት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ መገዛታቸውን ተናግረዋል፡፡
ድጋፉ በተለያዩ አካባቢዎች በዘርፉ የሚስተዋሉ መጠነ ሰፊ ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚያግዝ ነው የገለጹት፡፡
በተለይም የእናቶችና ጨቅላ ሕጻናት ጤና አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነትን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚያስችሉ አስረድተዋል፡፡
የአምቡላንስ ድጋፉ በእናቶችና ጨቅላ ሕጻናት ጤና አገልግሎት የተደራሽነት ክፍተት ላለባቸው ክልሎች መደረጉን አመልክተዋል፡፡
በአሸናፊ ሽብሩ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!