Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦቱን አጠናክሮ ያስቀጥላል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ፍሰት የቀጠለ በመሆኑ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በአዲሱ በጀት ዓመትም ተጠናክሮ ይቀጥላል አለ።

ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ በነገው ዕለት እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

ባንኩ ጨረታውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ ከውጭ ምንዛሪ ገቢ ከፊሉን ለባንኮች በጨረታ ማቅረቡ በባንኮች ዘንድ የሚኖረውን የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በመደገፍ የዋጋ እና የውጭ ምንዛሪ መረጋጋት እንዲፈጠር አስችሏል ብሏል።

ባንኩ ለነገው ጨረታ 150 ሚሊየን ዶላር ያዘጋጀ ሲሆን፤ በጨረታው የሚሳተፉ አካላት የጨረታ ሰነዳቸውን ከጠዋት 4 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት ድረስ ማስገባት እንደሚችሉ ገልጿል።

የጨረታ ውጤቱም በዕለቱ ቀን 9 ሰዓት ላይ ይፋ እንደሚሆን ነው የገለጸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.