ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኬንያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ራይላ ኦዲንጋ ባደረባቸው የልብ ሕመም ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡
አንጋፋው የኬንያ ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ በሕንድ ሀገር ሕክምናቸውን ሲከታተሉ እንደነበር ተመላክቷል፡፡