የጋምቤላ ክልል ከ1 ሺህ 500 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ አስገባ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋምቤላ ክልል ማዕድን ኤጀንሲ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ከ1 ሺህ 500 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ተደርጓል አለ፡፡
የኤጀንሲው ምክትል ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ገዳሙ እንዳሉት፤ በሩብ ዓመቱ 1 ሺህ 500 ኪሎ ግራም ወርቅ ገቢ ለማድረግ ታቅዶ ከዕቅድ በላይ ማሳካት ተችሏል።
በዚህም 1 ሺህ 588 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ተደርጓል ብለዋል።
ለብሔራዊ ባንክ ገቢ የተደረገው የወርቅ መጠን ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ682 ኪሎ ግራም ብልጫ ማሳየቱ ተመላክቷል፡፡
በክልሉ በበጀት ዓመቱ 6 ሺህ ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ለማቅረብ እየተሰራ ስለመሆኑም አብራርተዋል፡፡
መንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት ለብሔራዊ ባንክ የሚገባውን የወርቅ መጠንን ማሳደጉን ገልጸው፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ሕገ ወጥ የወርቅ ግብይት እንዲቀንስ አድርጓል ነው ያሉት፡፡
በክልሉ በዋናነት በአራት ወረዳዎች የወርቅ ማዕድን እንደሚመረትም ገልጸዋል።
በአብዱ ሙሃመድ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!