Fana: At a Speed of Life!

ሃብት ለማፈላለግ የሚያስችለው የንጋት ሐይቅ ማስተር ፕላን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ የተፈጠረው ንጋት ሰው ሰራሽ ሐይቅ ያለውን ዕምቅ አቅም አሟጥጦ ለመጠቀም የሚያስችል ማስተር ፕላን በዝግጅት ላይ ይገኛል።

የማስተር ፕላኑ ዝግጅት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስተባባሪነት የሚመለከታቸውን ባለድርሻዎችን በማሳተፍ እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።

በሚኒስቴሩ የተቀናጀ የውሃ ሃብት አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈፃሚ ደበበ ደፈርሶ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ የማስተር ፕላኑ ዓላማ የንጋት ሐይቅ የፈጠራቸውን ጸጋዎች በሥርዓት ለማስተዳደር ነው።

ማስተር ፕላኑ ቀጣይ የሚፈጠሩ ከተሞችን ታሳቢ በማድረግ የንጋት ሐይቅ የውሃ ሃብትና ከባቢውን በመጠበቅ የተፋሰሱን ሀገራት የውሃ ሃብት ዘላቂነት የሚያስጠብቅ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ሐይቁ ላይ ያለውን ውሃ ተከትሎ የተፈጠረው ስነ ምህዳር ትልቅ ሃብት በመሆኑ የዜጎችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚሳያድጉ የቱሪዝም፣ የዓሣ ሃብት፣ የትራንስፖርትና ተያያዥ ትሩፋቶች ይዞ መጥቷል ብለዋል።

የውሃ ሃብቱን ዘላቂ በሆነ መንገድ መጠበቅ እንደሚገባ ገልጸው÷ ይህም ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንድትሆን እና የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ከግድቡ በዘላቂነት ውሃ እንዲያገኙ ያስችላል ነው ያሉት።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ግዴታ የገባንባቸውን የውሃ አለቃቀቅ ህጎች መሰረት በማድረግ ሌሎች ልማቶችን በተሻለ መንገድ ማከናወን እንችላለን ሲሉም ገልጸዋል።

የንጋት ሐይቅ ማስተር ፕላን በአቅማችን የት ድረስ መሄድ እንደምንችል ያሳየናል ያሉት አቶ ደበበ÷ ማስተር ፕላኑን መሰረት ያደረገ የሃብት ማፈላለግ ስራ መስራት ይቻላል ብለዋል።

በሕዳሴ ግድብ ላይ የተፈጠረው በአፍሪካ 4ኛው ግዙፉ የንጋት ሐይቅ ከ70 በላይ ደሴቶች ያሉትና ከ74 ቢሊየን ሜትሪክ ኪዩብ በላይ ውሃ የያዘ ነው።

በአቢይ ጌታሁን

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.