የብልፅግና ፓርቲ በሁሉም ዘርፎችና መስኮች ስኬታማ ጉዞ እያደረገ ይገኛል – አቶ አደም ፋራህ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልፅግና ፓርቲ በሁሉም ዘርፎችና መስኮች ስኬታማ ጉዞ እያደረገ ይገኛል አሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ፡፡
የብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ መድረክ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በመድረኩ አቶ አደም ፋራህ÷ ፓርቲው በሁሉም ዘርፎችና መስኮች ስኬታማ ጉዞ እያደረገ እንደሚገኝ በመግለጽ የተመዘገቡ ስኬቶችን አብራርተዋል፡፡
ለኢትዮጵያና ለፓርቲው በሚመጥን መንገድ ከፍ ተደርጎ በመታቀዱ፤ በመደመር እሳቤ ሁሉንም አቅሞች ለመጠቀም ጥረት በመደረጉ በገቢር ነበብ እይታ በየአካባቢው ያለውን ተግባራዊ እውነታ መሰረት መደረጉ የፓርቲው ስኬት ምንጮች መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በተጨማሪም በፍጥነትና በፈጠራ መርህ በመሰራቱና ፈተናን ወደ ዕድል የመቀየር መርህ መከተል በመቻሉ ፓርቲው ዘርፈ ብዙ ስኬቶችንና ድሎችን አስመዝግቧል ብለዋል።
በመድረኩ በፓርቲውና በህዝብ ንቅናቄ የተሰሩ ስራዎች በጥልቀት የሚገመገሙ ሲሆን በሁሉም መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶችን ማስቀጠል እና ጉድለቶችን ለማረም የጋራ መግባባት ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል።