Fana: At a Speed of Life!

የአማዞን ኢንተርኔት መቋረጥ የተለያዩ አገልግሎቶችን አስተጓጎለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማዞን ኩባንያ ኢንተርኔት መቋረጡን ተከትሎ በርካታ መተግበሪያዎች እና ባንኮች አገልገሎት መስጠት አቁመዋል ተባለ፡፡

ስናፕቻት፣ ዶሊንጎ እና ሮብሎክስ በጊዜያዊነት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ መተግበሪያዎች መሆናቸው ነው የተገለፀው፡፡

በተጨማሪም ሎይድስ፣ ሃሊፋክስ እና ባንክ ኦፍ ስኮትላንድ በኢንተርኔት መቋረጡ ምክንያት ስራ ማቆማቸው ተገልጿል፡፡

በርካታ የባንክ እና የተለያዩ መተግበሪያዎች ደንበኞች በኢንተርኔት መቋረጥ ምክንያት አገልግሎት ማግኘት እንዳልቻሉ ሪፖርት እያደረጉ እንደሚገኙ ቢቢሲ ዘግቧል።

አማዞን አገልግሎቱ የተቋረጠበትን ምክንያት በማጣራት አስቸኳይ መፍትሔ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.