Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የፋይናንስ መሰረተ ልማትን ማዘመን ቅድሚያ የምትሰጠው ጉዳይ ነው – ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የፋይናንስ መሰረተ ልማትን ማዘመን ቅድሚያ የምትሰጠው ጉዳይ ነው አሉ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)፡፡

ከዓለም ባንክና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ዓመታዊ ጉባኤ ጎን ለጎን ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከአይኤምኤፍ የገንዘብ ድርጅት እና የካፒታል ገበያ ክፍል የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ በዋናነት የገንዘብ ፖሊሲ፣ የካፒታል ገበያ እና የፋይናስ መሰረተ ልማት ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ነው፡፡

ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በውይይቱ ወቅት የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ላይ ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለውን ዕድገት በተመለከተ ባደረጉት ገለጻ፤ ኢትዮጵያ የፋይናንስ መሰረተ ልማትን ለማዘመን ቅድሚያ የምትሰጠው ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ለውጥ እና ፖሊሲ ማስፈጸሚያ አቅምን ለመደገፍ ጠንካራ አጋርነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የካፒታል ገበያ ልማት እና የውጭ ምንዛሪ ሥርዓትን ማጠናከር ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች የኢትዮጵያን የገንዘብና የካፒታል ገበያ ማሻሻያ ለማስቀጠል፣ የፋይናንስ መረጋጋትን ለማጎልበት እንዲሁም የእውቀት እና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.