የጥፋት መንገዶችን ወደ ጎን በመተው ያለንን እምቅ ሃብት በሚገባ መጠቀም አለብን – አባዱላ ገመዳ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጥፋት መንገዶችን ወደ ጎን በመተው ያለንን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት በሚገባ መጠቀምና ማልማት አለብን አሉ የቀድሞ አመራር አባዱላ ገመዳ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሶፍ ኡመር ወግ በሚል ርዕስ ከቀድሞ እና በሥራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
አባ ዱላ ገመዳ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ባሌ ለአካባቢው ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ የሚበቃ እምቅ የተፈጥሮ ሃብት እንዳለው አውስተዋል፡፡
ይህን መሰል ሃብት ይዞ ማሕበረተሰቡ አስፈላጊው መሰረተ ልማት እንደሌለውና በአስከፊ ድህነት ውስጥ የሚኖር መሆኑ እንደሚያስቆጭ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በባሌ ዞን የሚኖሩ በርካታ ወጣቶች በሕገ ወጥ መንገድ ስደትን በመምረጥ ለከፍተኛ ጉዳት እንደሚዳረጉ አንስተዋል፡፡
በሌላ በኩል ይሄን የመሰለ ሃብት ይዘን በሚገባ አልምቶ ከመጠቀም ይልቅ ጊዜያችን የምናሳልፈው በመጨቃጨቅ፣ በንትርክና በመዋጋት መሆኑ የሚቆጨኝ ጉዳይ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አሁን ላይ የተጀመረው ሥራ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመው ÷ በቀጣይ ከጭቅጭቅ፣ከንትርክና ከመታኮስ ወጥተን ሙሉ አቅማችን ተጨባጭ የልማት ሥራ ላይ ማዋል አለብን ነው ያሉት፡፡
የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥን፣ ከድህነት ለመውጣት እና መጪው ትውልድ በሀገሩ የሚኮራ እና ተጠቃሚ የሚሆንበትን ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት መስራ ይገባል ብለዋል፡፡
ከዚህ ውጪ ያለው መንገድ የጥፋት መንገድ መሆኑን የተናገሩት አባ ዱላ ገመዳ ÷ ያለውን የሰው ሃይል፣ ሃብትና እምቅ አቅም በመጠቀም ያለንን የተፈጥሮ ሃብት ማልማት ይገባል ብለዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!