Fana: At a Speed of Life!

ችግሮችን በመቻቻልና በውይይት በመፍታት የልማት ሥራዎችን ማጠናከር ይገባል – ሌ/ጄ ጻድቃን ገ/ትንሳኤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ችግሮችን በውይይት በመፍታትና ሰላምን በማስጠበቅ የልማት ሥራዎችን ማጠናከር ይገባል አሉ ሌተናል ጄነራል ጻድቃን ገብረ ትንሳኤ ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሶፍ ኡመር ወግ በሚል ርዕስ ከቀድሞ እና በሥራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ሌ/ጄ ጻድቃን ገ/ትንሳኤ በዚህ ወቅት ÷በጉብኝታቸው የተመለከቱት ነገር ፈጽሞ ከገመቱት በላይ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ጉብኝቱ ከረጅም ጊዜ በኋላ ከቀድሞ የሥራ እና የትግል ጎደኞቻቸው ጋር አብሮ ጊዜ የማሳለፍና የመምከር እድል እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡

የባሌ ዞንን ከዚህ ቀደም እንደሚያውቁት አስታውሰው÷ ይሁን እንጂ የአሁኑ ጉብኝት ያለውን እምቅ ሃብት በሚገባ መረዳት እንዳስቻላቸው አንስተዋል፡፡

የሶፍ ኡመር ዋሻ አስደናቂ የተፈጥሮ ሃብት ነው፤ አሁን ላይ እየለማበት ያለው መንገድ የሚበረታታ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

ከባሌ ተራራ የሚመነጩት ወንዞች ለማንኛውም ልማት የተዘጋጁ መሆናቸው ጠቁመው÷ ይህም ትልቅ ተስፋ ያጭራል ነው ያሉት፡፡

በአካበቢው እየለማ የሚገኘው በርካታ መሬት በቀጣይ ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች በር ከፋች መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ስሆነም ሰላማችንን ጠብቀን፣ እየተቻቻልንና የፖለቲካ ሥርዓታችንን አስተካክለን ችግር በሚፈታ መንገድ ከሄድን ቀጣዩ ጊዜ መልካም እድል ይዞ እንደሚመጣ እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ከችግሮቻችን አልወጣንም ፤ ችግሮችንም በመቻቻል፣ የፖለቲካ ሥርዓታችን በማስተካከልና ለሀገር በሚጠቅም መልኩ መፍታት ይገባል ነው ያሉት፡፡

የኢኮኖሚ ሥርዓታችን እየተሻሻለ ሲሄድ የፖለቲካ ሥርዓታችን የበለጥ ይጠናከራል፤ ችግሮችንም በሒደት መፍታት ይገባል፤ አሁን ያለው ሁኔታም ተስፋ ሰጪ ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.