Fana: At a Speed of Life!

ደረጃውን ለጠበቀ የሎጂስቲክስ አገልግሎት የዘመነ የባቡር ስርዓትን እውን ማድረግ ይገባል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሎጂስቲክስ አገልግሎት እንዲኖራት የዘመነ የባቡር ስርዓትን እውን ልታደርግ ይገባል አለ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር።

በኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የተዘጋጀው ብሔራዊ የባቡር ቢዝነስና ኢንቨስትመንት ጉባዔ እየተካሄደ ይገኛል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ዳንጌ ቦሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ሎጂስቲክስ ሀገርን ወደፊት በማንቀሳቀስ ዘላቂ ኢኮኖሚ ለመገንባት መሰረት ነው።

ባቡር ወጪ ቆጣቢ ብቻ ሳይሆን ኢንዱስትሪዎችን እርስበርስ እንዲገናኙ በማድረግ አቅማቸውን የማሳደግ አቅም እንዳለው ገልጸው÷ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሎጂስቲክስ አገልግሎት እንዲኖራት የዘመነ የባቡር ስርዓትን እውን ልታደርግ ይገባል ብለዋል።

ግባችን ዘላቂነት ያለው ዘመናዊ የባቡር ስርዓት መገንባት ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው÷ ኢንቨስተሮች በዘርፉ መሰማራት እንዲችሉ የተመቻቸ ሁኔታ መፈጠሩን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ህሊና በላቸው (ኢ/ር) በበኩላቸው÷ ዘርፉን ለማሳደግ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መሰረተ ልማቶችን የማሟላት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ሀገር አቀፍ በሆነ መልኩ ኢንዱስትሪዎችን የሚያገናኝ የባቡር መሰረተ ልማት ማሳደግ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።

በመድረኩ የተገኙት በአፍሪካ ሕብረት የመሰረተ ልማትና ኢንጂነሪንግ ኮሚሽነር ሌራቶ ማታቦሜ አኅጉር አቀፍ የባቡር መሰረተ ልማት በመዘርጋት አፍሪካዊያን ግንኙነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ በባቡር ዘርፍ የምታከናውናቸው ስራዎች ለሌሎችም ምሳሌ የሚሆንና አፍሪካ መሰረተ ልማቶቿን በራሷ ማሟላት እንደምትችል ማሳያ እንደሚሆን አንስተዋል።

ባቡር አፍሪካ ያስቀመጠቻቸውን ግቦች ለማሳካት ዋና ሞተር እንደሆነም በመግለጽ ሀገራት ለዘርፉ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው አመላክተዋል።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.