በሙከራ ላይ ያለው የቻይና ፈጣኑ የኤሌክትሪክ ባቡር…
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቻይና ሲአር450 የሚል ስያሜ የሰጠችውን የዓለም ፈጣን የኤሌክትሪክ ባቡር በሙከራ ላይ አውላለች፡፡
ባለጥይት ፍጥነት ባቡር የተባለው የዓለም ፈጣኑ ባቡር በአሁኑ ሰዓት በቻይና ሻንጋይ ቼንግዱ የባቡር መስመር ላይ የጉዞ እንቅስቃሴ ሙከራ እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
ፈጣኑ ባቡር በሙከራ ላይ በሰዓት 350 ኪሎ ሜትር መጓዝ የቻለ ሲሆን÷ ማሻሻያ ተደርጎለት ሙከራውን ሲያጠናቅቅ በሠዓት 450 ኪሎ ሜትሮችን መጓዝ ይችላል ተብሏል፡፡
ፈጣኑ ባቡር ቀደም ሲል በቻይና ይፋ ከተደረገው የፉክሲንግ ፈጣን ባቡር በ100 ሴኮንዶች ፍጥነት የሚበልጥ እንደሆነና ይህም በዓለም ፈጣን ባቡር እንዲሆን እንዳስቻለው ተመላክቷል፡፡
የሲአር450 ፈጣን ፕሮጀክት በቻይና በፈረንጆቹ 2021 የተጀመረ ሲሆን÷ በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ ተመርቆ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡
ይህም ቻይና የዓለም ፈጣን ባቡር ፕሮጀክት መሪነትን እንድታሰፋ ያደርጋታል መባሉን ኢሲኤንኤስ እና ሲጂቲኤን ዘግበዋል፡፡
በሚኪያስ አየለ