Fana: At a Speed of Life!

የየም ባህላዊ መድኃኒቶች ለቀማ “ሳሞ ኤታ”

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገር በቀል እውቀቶችን በጥቅም ላይ ለማዋል እየተሰራ ነው አለ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ብሔረሰብ ባህላዊ መድኃኒቶች ለቀማ “ሳሞ ኤታ” በቦር ተራራ ላይ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማህዲ በመርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት÷ ሀገር በቀል ዕውቀቶችን በማልማት ጥቅም ላይ ለማዋል እየተሰራ ነው።

በየዓመቱ ጥቅምት 17 የሚካሄደው የየም ብሔረሰብ ባህላዊ መድኃኒት “ሳሞ ኤታ” ለቀማና ቅመማ ሥርዓት የኢትዮጵያን ባህላዊ ሀብት ለመጠበቅ የሚደረገውን ጥረት የሚያሳይ እንደሆነ አንስተዋል።

የየም ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ሞጋ በበኩላቸው÷ በቦር ተራራ የሚገኙ ዕፅዋት ለሰው ብቻ ሳይሆኑ ለእንሰሳትም እንደሚያገለግሉ በሕብረተሰቡ ዘንድ ይታመናል ብለዋል።

”ሳሞ ኤታ” ትርጉሙ የከረመ መድኃኒት ማለት ሲሆን÷ የም በዕፅዋት ጥበብ አስቀድሞ በሽታን የሚከላከልና የሚያስወግድ እንዲሁም ፈውስን ከገጸ ምድር በረከት የሚያገኝ ጥበበኛ ሕዝብ እንደሆነም አመላክተዋል።

በዛሬው ዕለት የአካባቢው ነዋሪዎች በተራራው ላይ ካሉ በርካታ የእፅዋት አይነቶች ቅጠላቸውን፣ ስሮቻቸውን እና ቅርፊታቸውን እንደሚሰበስቡም አስረድተዋል።

በጥቅምት 17 ቀን የሚካሄደው የባህል መድኃኒት ለቀማ ሁሉም የማሕበረሰብ ክፍል በመሳተፍ ከአባቶችና እናቶች እውቀት እንደሚቀስሙ ገልጸው÷ የተሰበሰበውን መድኃኒት በአግባቡ በማዘጋጀት ለሰውና ለእንስሳት ጥቅም ላይ እንደሚውል አብራርተዋል።

የባህል መድኃኒት የሚለቀመው በጥቅምት ወር ብቻ እንደሆነ እና በዕለቱ የሚለቀመውም የባህል መድኃኒት ከ200 በላይ ለሚሆኑ በሽታዎች ፍቱን መድኃኒት እንደሚሆኑ የብሔረሰቡ የባህል መድኃኒት አዋቂዎች ተናግረዋል።

በተስፋሁን ከበደ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.