Fana: At a Speed of Life!

ምርታማነት እያደገ ሲሄድ ገበያ ይረጋጋል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምርታማነት እያደገ ሲሄድ ገበያ ይረጋጋል፤ ገቢ ይጨምራል፤ ከውጪ የሚገቡ ምግቦችን በመቀነስ የመላክ አቅማችን ያድጋል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት በምስራቅ ሸዋ ዞን የክረምት ስንዴ ምርት አሰባሰብን በመጎብኘት የበጋ ስንዴ ሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሂደዋል።

ጉብኝታቸውን ተከትሎ በሰጡት ሐሳብ እንዳሉት÷ የግብርና ስራዎች ተስፋ የሚሰጡ ናቸው።

አርሶ አደሮች የኑሮ ደረጃቸውንና ቤታቸውን ማሻሻልና የእርሻ ስራ ውጤቶች በሕይወታቸው ላይ በተግባር መታየት እንዳለበት ገልጸዋል።

የማዕድን ዘርፍ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ እና ኢንዱስትሪውም በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መሆኑን አንስተዋል።

እነዚህን አስተሳስረን ምርታማነትን በማሳደግና ሃብት በመፍጠር አርሶ አደሩ የሚጠቀምበትን መንገድ ካመቻቸን ኢትዮጵያ ተለውጣ በአዲስ ቁመና የመታየቷ ጉዳይ ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።

አርሶ አደሩ ብር በባንክ የማስቀመጥ ልምዱ እያደገ መምጣቱን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ የኑሮ ደረጃቸውንና ቤታቸውን ማሻሻልና ማገዝ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

አቅም ያላቸው አርሶ አደሮች በገጠር የተገነቡ ሞዴል ቤቶችን መሰረት በማድረግ ዘመናዊ ቤቶችን መሥራት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።

ሁሉንም ዘርፎች በሚዛን ማስኬዳችን በተጨባጭ የፖሊሲ ትሩፋት እያመጣ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ ዋና ዋና ዘርፎችን ይዘን ሌሎች ዘርፎች እየተሰናሰሉ እንዲወጡ እያደረግን ስለሆነ እንስራ እንበርታ ሲሉ አስገንዝበዋል።

ከአልባሌ ቦታ ወጥተን በስራና በትጋት ብቻ ውጤት ለማምጣት እንጣር በማለትም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.