ወጣቱ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ተሳትፎውን እንዲያጠናክር ተጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ወጣቱ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ያለውን ተሳትፎ ይበልጥ ማጠናከር አለበት አለ።
‘አስተማማኝ ሰላም ለሀገር ማንሰራራት’ በሚል መሪ ሀሳብ የወጣቶች የንቅናቄ መድረክ በዛሬው ዕለት በነቀምቴ ከተማ ተካሂዷል።
የክልሉ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ከድር እንዳልካቸው ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በክልሉ የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም ለማጽናት ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመቀናጀት እየተሰራ ነው።
በዚህም የወጣቶች ሚና የላቀ መሆኑን ገልጸው÷ የሰላም መስፈን የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል።
በመሆኑም ወጣቱን ያሳተፈ ሰላምን የማጽናት ተግባር ትኩረት እንደተሰጠው አቶ ከድር ተናግረዋል።
ሰላም ሲረጋገጥ የወጣቱ ስራ ዕድል ተጠቃሚነት እንደሚጨምር ገልጸው÷ አሁን ላይ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በተለያዩ የመንግስት የልማት አጀንዳዎች ወጣቶች ተጠቃሚ የሆኑበት ሁኔታ መፈጠሩን አንስተዋል።
በንቅናቄ መድረኩ የተሳተፉ ወጣቶች በአካባቢያቸው አንጻራዊ ሰላም በመስፈኑ የሰላም ዋጋ ከፍተኛ እንደሆነ መገንዘባቸውን ገልጸዋል።
በአካባቢያቸው የመጣውን ሰላም በዘላቂነት ለመጠበቅም መንግስትን ጨምሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!