Fana: At a Speed of Life!

የኒውክሌር ኃይል የሁለንተናዊ ብልፅግናችንን ጉዞ የሚደግፍ ነው – ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኒውክሌር ኃይል ሁለንተናዊ ብልፅግናችንን እውን ለማድረግ የምናደርገውን ጉዞ የሚደግፍ ነው አሉ የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)።

ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት÷ የኒውክሌር ኃይል ለጤና፣ ግብርና እና ኢንዱስትሪ ዘርፎች እንቅስቃሴ መሳለጥ ትልቅ አቅም የሚስገኝ ነው፡፡

ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይልን የምትጠቀመው ለሰላማዊ የልማት እንቅስቃሴ መሆኑን ገልጸው÷ ብልፅግናን ይበልጥ ከፍ ለማድረግ የሚጠቅም እንደሆነም አመላክተዋል።

በኃይል አቅርቦት ችግር የሚገጥመውን የኢኮኖሚና የእድገት ፍላጎትን ለማሳካት የኒውክሌር ኃይል ተጨማሪ የልማት ሞተር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የኃይል አቅምን ለመገንባት ኒውክሌርን እንደ አማራጭ መውሰዷን የጠቆሙት ቢቂላ (ዶ/ር)÷ የሀገሪቱን ጸጋ ተጠቅሞ ማደግና መለወጥን በማለም የተጀመረው ይህ ፕሮግራም በኃይል እጥረት የሚዘጉ ኢንዱስትሪዎችን ይታደጋል ነው ያሉት፡፡

የኒውክሌር ፕሮግራም ኢትዮጵያዊያን ከድህነት ወጥተው የተሳካ ሁለንተናዊ ብልፅግናቸውን እንደሚያረጋግጡ ማሳያ እንደሆነ አመላክተዋል።

የኒውክሌር ኃይል ፕሮግራም ኢትዮጵያዊያንን የሚያሰባስብና ከድህነት ለመውጣት የሚደረገውን ጉዞ የሚደግፍ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የኃይል አማራጮቿን በማስፋት ምጣኔ ሃብታዊ እድገቷን ለማፋጠን ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየሰራች እንደምትገኝም ጠቁመዋል።

በወንድማገኝ ፀጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.