Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በድንበር ተሻጋሪ ወንዞቿ ያላት አቋም ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው – ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በድንበር ተሻጋሪ ወንዞቿ ያላት ጽኑ አቋም ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው አሉ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)።

“ውሃና ንጹህ ኢነርጂ ለዘላቂ እድገት” በሚል መሪ ሐሳብ ከጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሳምንት ዛሬ ይጠናቀቃል።

በሳምንቱ መርሐ ግብር በውሃ ሃብት ዘርፍ በተገኙ ስኬቶች፣ መሻሻል ስለሚገባቸውና ቀጣይ ርምጃዎች ላይ ያተኮሩ ውይይቶች ተደርገዋል።

የዛሬውን መርሐ ግብር ያስጀመሩት ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ በድንበር ተሻጋሪ ወንዞቿ ያላት ጽኑ አቋም የቀጣናውን ተገቢ፣ ሚዛናዊ እና ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው ብለዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት የጎርፍ አደጋ ስጋት ማስቀረትን ጨምሮ የተለያዩ በረከቶችን ይዞ መምጣቱን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ የማይበገር አካባቢ የመፍጠር ዕድል እንዳለውም ጠቁመዋል።

ወንዞቻችንን አልምተን ለመጠቀም የጀመርናቸው እንቅስቃሴዎች ውሃን በፍትሀዊነትና በተገቢነት የመጠቀም አቋማችንን የሚገልጽ ነው ብለዋል።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.