Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ሁለቱ ኮሪያዎች ወደ ንግግር እንዲመለሱ እንድታግባባ ተጠየቀች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ሊ ጄ ምያንግ ሀገራቸው ከሰሜን ኮሪያ ጋር ስታደርጋቸው የነበሩ ድርድሮች እንዲቀጥሉ ቻይና ድጋፍ እንድታደርግ ጠይቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከእስያ ፓስፊክ የኢኮኖሚ ትብብር ጉባኤ ጎን ለጎን ከቻይና አቻቸው ሺ ጂንፒንግ ጋር ባደረጉት ውይይት በሀገሮቻቸው መካከል ያለውን ትብብር ለማሳደግ ተስማምተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሊ ጄ ምያንግ በዚሁ ወቅት፥ ተቋርጦ የቆየው የሁለቱ ኮሪያዎች ድርድር እንዲቀጥል ቻይና ሰሜን ኮሪያን እንድታግባባ ጠይቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሊ የኮሪያ ልሳነ ምድርን ከኒውክሌር የጦር መሳሪያ ነጻ ለማድረግ ያስችላል ያሉትን ስትራቴጂ ለፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ማስረዳታቸውን የፕሬዚዳንቱን የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጠቅሶ አሶሺየትድ ፕረስ ዘግቧል፡፡

ቻይና ሰሜን ኮሪያን በማግባባት በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል ሲደረጉ የነበሩ የድርድር ሂደቶች እንዲቀጥሉ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንድታደርግም ነው ፕሬዚዳንት ሊ የጠየቁት፡፡

ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በበኩላቸው፥ በሴኡል እና ፕዮንግያንግ መካከል ያለው አለመግባባት እልባት እንዲያገኝና በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን ጥረታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.