Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የድህረ ምርት ብክነትን ለመቀነስ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የድህረ ምርት ብክነትን ለመቀነስ በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ፡፡

በቢሮው የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር ምህረቱ መኮንን ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በክልሉ በመኸር እርሻ 1 ነጥብ 57 ሚሊየን ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች ተሸፍኗል፡፡

ከዚህም 56 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ጠቅሰው ÷ ለመኸር ሰብል ስብሰባ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን አመልክተዋል፡፡

ከምርት ስብሰባ ጀምሮ የድህረ ምርት ብክነትን ለመቀነስ በክልሉ የ90 ቀናት ንቅናቄ ተዘጋጅቶ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ መሰረትም አርሶ አደሩ የተሻሻሉ የምርት መሰብሰቢያ መሳሪያዎችን እንዲጠቀም የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

አርሶ አደሮች ምርትን በብረት ጎተራዎች እንዲሁም ጥራትና እውቅና ባላቸው ከረጢቶች እንዲያስቀምጡ የግብርና ባለሙያዎች ድጋፍና ክትትል እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በመኸር እርሻ ከለማ አትክልት እና ፍራፍሬ እስካሁን 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንትል በላይ ምርት መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡

የመኸር ሰብል ስብሰባ ሥራን አርሶ አደሮች በተገቢ ጥንቃቄ ማከናወን እንዳለባቸውም አቶ ምህረቱ አስገንዝበዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.