Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የደረሱ ሰብሎች ከብክነት ነፃ በሆነ መንገድ እየተሰበሰበ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የደረሱ የመኸር ሰብሎችን ከብክነትና ጥራት ጉድለት ነፃ በሆነ መንገድ እየተሰበሰበ ነው አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ኡስማን ሱሩር ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ ምርታማነትን ለማሳደግ ከሚሰሩ ስራዎች መካከል ድህረ ምርት ብክነትን መቀነስ አንዱ ነው።

በዚህም ድህረ ምርት ብክነትን ለመቀነስ የባለድርሻ አካላት የተቀናጀና የተናበበ ጥረት እንደሚያስፈልግ በመግባባት በግብርና የተሰማሩ ባለሃብቶችና የግብርና ሜካናይዜሽን ማሽን አካራዮች በቅንጅትና ትብብር እየሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በክልሉ በመኸር እርሻ 579 ሺህ 532 ሄክታር በዘር መሸፈኑን ገልጸው÷ 54 ሚሊየን 802 ሺህ 745 ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን ተናግረዋል።

አሁን ላይ የደረሱ ሰብሎችን የመሰብሰብ ስራው እየተከናወነ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ኡስማን እስካሁን ከ76 ሺህ 811 ሄክታር መሬት የተለያዩ የሰብል ምርቶች መሰብሰባቸውን አብራርተዋል።

በሁሉም ማሳዎች ያለው ሰብል የተሻለ የምርታማነት ቁመና ላይ መሆኑንም አመላክተዋል።

የደረሱ ሰብሎችን የመሰብሰብ ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን አንስተው÷ ምርቶቹን ያለብክነትና በጥራት ለመሰብሰብ በሚደረገው ጥረት የግብርና ባለሙያዎችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.