Fana: At a Speed of Life!

ያለ ባሕር በር ኑሩ ማለት ፍርደ ገምድል ነው – አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለ ባሕር በር ኑር ማለት ፍርደ ገምድል ነው አሉ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር)፡፡

ይህንን ፍርደ ገምድል አስተሳሰብ ሰላማዊ በሆነ መልኩ በመነጋገር መፍታት እንደሚያስፈልግ አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) ከፋና ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

ባሕር በር ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሚጠይቀውና በኢ-ፍትሐዊ መንገድ ያጣንበት ነው ብለዋል።

ለፖለቲካ ጥቅም እና ስልጣን ለማስጠበቅ ሲሉ ጥቂት ሰዎች የባሕር በሩን አሳልፈው እንደሰጡ ገልጸው÷ በወቅቱ ዓለም በትዝብት ይመለከታቸው እንደነበርም አስታውሰዋል።

ስልጣን ለማስጠበቅ የሻዕቢያ ድጋፍ ያስፈልገናል የሚለው ሐሳብ አዕምሯቸው ውስጥ ተቀርጾ የባሕር በሩን እንደ ጉዳይ አላዩትም ነው ያሉት፡፡

ለፖለቲካ ጥቅም ሲባል ዓለም የሚደግፈውን፣ ታሪክ የሚመሰክረውንና ሕጋዊ አግባብ ያለውን የሕዝብ ጥቅም አሳልፎ መስጠት ክህደት እንደሆነም አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከጥንት አክሱም ሥርወ መንግስት ከአዶሊስ ወደብ ጀምሮ ከቀይ ባሕር ጋር የተገናኘ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያላት ሀገር መሆኗንም አመላክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ በሰላም፣ በታሪክ እና በሕግ አውድ ታይቶ ሊፈታ የሚችል እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

በብርሃኑ አበራ

አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) ከፋና ፖድካስት ጋር የነበራቸውን ቆይታ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ👇
https://www.youtube.com/watch?v=5onYwmyM2M0

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.