Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በካካዎ ምርት የላቀ ውጤት ማምጣት የሚያስችል አቅም አላት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ኢትዮጵያ በካካዎ ምርት የላቀ ውጤት ማምጣት የሚያስችል አቅም አላት አለ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ንጉሴ ደቻሳ (ፕ/ር) ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ በውጭ ገበያ ተፈላጊነት ያላቸው እና ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑ ሰብሎችን ጨምሮ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ሰብሎች ምርታማነት ማሳደግ የሚያስችል ምርምር እየተካሄደ ነው።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያለውንና በኢትዮጵያ የማይታወቀውን የካካዎ ሰብል ለማላመድ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸው፤ በኢንስቲትዩቱ የቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል አማካኝነት የካካዎ ሰብል ምርምር እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል።

በዚህም ቸኮሌትን ጨምሮ የተለያዩ ጣፋጭ የምግብ ሸቀጦችን ለማምረት በግብዓትነት የሚያገለግለውን ካካዎ በኢትዮጵያ ለማምረት የሚያስችል ከፍተኛ አቅም እንዳለ መታየቱን ገልጸዋል።

ለኢትዮጵያ አየር ንብረት ምቹ የሆነ የካካዎ ዝርያ በምርምር መፍለቁን ጠቅሰው፤ በሰርቶ ማሳያ ደረጃ ከፍተኛ ምርት ማግኘት እንደሚቻል መረጋገጡን ጠቁመዋል።

ይህንን ተሞክሮ ወደ አርሶ አደሩ እና ሌሎች አምራቾች ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ በስፋት እየተሰራበት እንደሆነ ተናግረዋል።

የቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል ከ32 ሺህ በላይ የካካዎ ችግኝ አዘጋጅቶ በ2017 ዓ.ም የክረምት ወቅት ለአርሶ አደሩ ማቅረቡ ይታወሳል።

የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የሆኑት ኮትዲቯር፣ ጋና፣ ካሜሩን እና ናይጄሪያ በካካዎ አምራችነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ይታወቃሉ።

በአቢይ ጌታሁን

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.