መንግሥት ብሔራዊ ጥቅም እንዲከበር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው – አቶ ከበደ ዴሲሳ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግሥት የሀገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም እንዲከበር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው አሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ።
ሚኒስትር ዴኤታው ከፋና ፖድካስት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት÷ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ የመንግሥት ኃላፊነት ብቻ ተደርጎ መወሰድ የለበትም።
የብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ ስልጣን ይዞ ሀገርን የሚመራ ፓርቲ ወይም መንግሥት ሳይሆን ዘመን ተሻጋሪ የዜጎች ዋና አጀንዳ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በማሳደግ ብሔራዊ ጥቅምና ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን እንዳታስከብር ባዕዳን ወራሪዎች ለዘመናት ችግር ሲፈጥሩ መቆየታቸውን አንስተው÷ በተለያዩ ወቅቶችም የዓባይን ምንጭ ለመያዝ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር አስታውሰዋል።
ይሁን እንጂ ኢትዮጵያዊያን በአንድነትና በጋራ ትግል የጠላቶችን ሴራ በማክሸፍ ዓባይን በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ለብሔራዊ ጥቅም ማዋል እንደቻሉ ተናግረዋል።
ዜጎች በሀገር ጉዳይ ያለ ምንም ልዩነት አብረው መቆማቸው ለብሔራዊ ጥቅም መከበር ዓይነተኛ ተምሳሌት እንደሆነም አውስተዋል።
በቀደሙ መንግሥታት ከብሔራዊ ጥቅም ይልቅ የቡድን ጥቅሞችን ማስቀደም ሀገሪቱን ወደኋላ እንደጎተታት ጠቅሰው÷ አሁን ላይ መንግሥት የሀገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም እንዲከበር ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።
በዚህም የባሕር በርን ጉዳይ ከታሪክ፣ ከህግና ከመልከዓ ምድራዊ አቀማመጥ በመነሳት የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ መንግሥት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ዜጎች ሊደግፉትና የሚጠበቅባቸውን ሊያበረክቱ እንደሚገባም አጽንዖት ሰጥተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!