Fana: At a Speed of Life!

የሰሜን ዕዝን ጥቃት የምናስታውሰው መቼም እንዳይደገም ነው – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሰሜን ዕዝን ጥቃት የምናስታውሰው መቼም እንዳይደገም ነው አሉ።
በሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት የተፈፀመበት 5ኛ ዓመት “እንዳይደገም ፤ መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ሃሳብ እየታሰበ ነው፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በመርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ÷ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈፀመው ጥቃት መቼም የማይረሳ እንደሆነ ተናግረዋል።
የሰሜን ዕዝ በትግራይ ክልል ለዓመታት የክልሉን ሕዝብ ከሻዕቢያ ትንኮሳ ሲጠብቅ ከመቆየቱም ባሻገር በገንዘቡ፣ በጉልበቱና በእውቀቱ ሲደግፍ እንደነበር አስታውሰዋል።
እንዲህ ባለው ሠራዊት ላይ የተፈፀመው ጥቃት በኢትዮጵያ ታሪክ ጥቁር ጠባሳ የጣለ እና አንገት የሚያስደፋ ታሪክ ጽፎ ያለፈ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት፡፡
ሀገር ለማቆየት በየጊዜው መስዋዕትነት ተከፍሏል ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ÷ የሰሜን ዕዝን ልዩ የሚያደርገው በገዛ ወገኖቹ የጭካኔ ተግባር የተፈፀመበት በመሆኑ ነው ብለዋል።
በሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት በየዓመቱ የምናስታውሰው መቼም እንዳይደገም ነው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።
በሰሜን ዕዝ ላይ ስለተፈጸመው የጭካኔ ተግባር ሲወሳ ስለጥቂት የሕወሃት አባላት ክህደት መሆኑን ጠቁመው ÷ ይህ ቡድን አሁንም የሀገር ጠላት ሆኖ መቀጠሉን አመልክተዋል፡፡
በአንዷለም ተስፋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.