ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ የንግድ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ የንግድ ግንኙነታቸውን ለማስፋትና ለማጠናከር ተስማምተዋል።
የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ከፈረንሳይ የውጭ ንግድና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ተወካይ ኒኮላስ ፎሪሲየር ጋር ባደረጉት ውይይት÷ የሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብርን በይበልጥ ማሳደግና ተጨማሪ የፈረንሳይ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ መክረዋል።
ሀገራቱ በዘላቂና ሁሉን አቀፍ እድገት ላይ ያላቸውን ትብብር ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆናቸውን በመግለጽ በኢንዱስትሪ ልማት፣ ታዳሽ ኃይል፣ መሠረተ ልማት፣ የግብርና ማቀነባበሪያና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ጨምሮ በሌሎች ዘርፎች በትብብር እንደሚሰሩ አመላክተዋል።
አቶ አሕመድ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፉን በይበልጥ ለማሻሻል ፖሊሲን ጨምሮ ተቋማዊ ሪፎርሞች የማድረግ ስራዎችን እየሰራች ነው።
ይህም በዘርፉ ቀጣይነት ያለውን ዓለም አቀፍ ተሳትፎ ከማሳደግ ባለፈ ቀልጣፋና ምቹ አገልግሎት ለማግኘት እንደሚያስችል አስረድተዋል።
የኢትዮጵያን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካት የኢኮኖሚ ትስስሩን ማስፋትና ማጠናከር እንደሚገባ በመግለጽ÷ ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ የልማት ተነሳሽነት ላደረገችውና እያደረገች ላለው ድጋፍ አመስግነዋል።
ኒኮላስ ፎሪሲየር በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ አድንቀው፤ ፈረንሳይ በቀጣይም የንግድ ትስስሩን ለማስፋት፣ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ብሎም የኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።
በፈረንጆቹ ግንቦት 2026 የፈረንሳይ ልዑክ ወደ ኢትዮጵያ በሚያደርገው ይፋዊ ጉብኝት ሁለቱም ወገኖች ውይይቱን ለመቀጠል ተስማምተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!