Fana: At a Speed of Life!

ፌዴሬሽኑ የአፍሪካ ባህል ስፖርቶች ኮንፌዴሬሽን አባልነት ማረጋገጫ ተሰጠው

‎አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን አባል የሆነበትን የአፍሪካ ባህል ስፖርቶች ኮንፌዴሬሽን የአባልነት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት በዛሬው ዕለት ተሰጠው።

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ህይወት መሃመድ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ÷ ጥያቄው አስቀድሞ ተቀባይነት ማግኘቱን ጠቅሰው÷ በዚምባብዌ ሃራሬ ከተማ በተካሄደው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ የማረጋገጫ ሰርቲፊኬት መረከባቸውን ተናግረዋል።

‎አባልነቱ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ድንበር ተሻጋሪ የሆነ ግንኙነቶችን በመፍጠር ባህላዊ ስፖርቶቻችንን ለማስተዋወቅ ይረዳል ብለዋል።

‎በ1977 ዓ.ም የተመሰረተው የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን የኢትዮጵያዊያን ባህላዊ ስፖርቶችና ጨዋታዎች በጥናትና ምርመር በመለየት ይዘታቸውን ጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ የማስተዋወቅ ስራዎችን እየሠራ ይገኛል።

በሙባረክ ፋንታው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.