በቡታጅራ ከተማ በብልጽግና ፓርቲ ውህደት እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት እየተደረገ ነው
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቡታጅራ ከተማ በብልጽግና ፓርቲ ውህደት እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።
ውይይቱ በከተማዋ በሚገኙ ቀበሌዎች ተከፋፍሎ እየተካሄደ ይገኛል።
የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ባሳተፈው ውይይት በፓርቲው ፕሮግራም ላይ ምክክር እየተደረገ ነው።
ከዚህ ባለፈም በውህድ ፓርቲው አስፈላጊነትና ለሃገር አንድነት በሚኖረው ፋይዳ ላይም ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ ላይ ፓርቲው አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ከመፍጠር አንጻር ጠቀሜታ እንዳለው ተነስቷል።
ውህድ ፓርቲው በቀጣይ ለዴሞክራሲ ግንባታ፣ እኩል ተጠቃሚነት እና እድገት ስለሚኖረው ፋይዳ በውይይቱ ላይ ተነስቷል።
በታሪኩ ለገሰ