Fana: At a Speed of Life!

ኦቪድ ሪል ስቴት የሽያጭ ኤክስፖ ሊያዘጋጅ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኦቪድ ሪል ስቴት ታላቅ የሽያጭ ኤክስፖ ሊያዘጋጅ ነው።

ድርጅቱ በገርጂ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ በአራት ኪሎ ጥይት ቤት፣ በጎልፍ ክለብ፣ በኢትዮ ኩባ እና ገላን ጉራ አምስት የግንባታ ሳይቶች የሚገኙ ቤቶችን ነው በኤክስፖው የሚያቀርበው።

የድርጀቱ የማርኬቲንግ ማናጀር መቅደስ ቀደመ እንዳሉት÷ በርካታ ፕሮጀክቶችን ገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ የሚታወቀው ኦቪድ ሪል ስቴት ከሕዳር 22 እስከ ታሕሣሥ 6 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርጓል።

ቤቶቹ ግንባታቸው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቆ የቤት ዕቃ የተሟላላቸው እና በከፊል ግንባታዎች የተጠናቀቁ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡

ቤቶቹ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ታሳቢ እንዳደረጉ ጠቅሰው÷ አሁን የተደረገው የዋጋ ቅናሽ ከዚህ ቀደም ከተደረጉት ቅናሾች ከፍተኛው ቅናሽ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቤቶቹ ከታሕሣሥ 7 በኋላ የዋጋ ማስተካከያ እንደሚደረግባቸው ገልፀው፤ ደንበኞች በተመጣጣኝ ዋጋ በመግዛት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በዙፋን አምባቸው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.