በሀረሪ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ስራ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀረሪ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በዛሬው ዕለት ተመርቆ ስራ ጀምሯል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እና የሲቪል ሰርቪስ ምክትል ኮሚሽነር አልማዝ መሰለ ማዕከሉን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
በማዕከሉ ሰባት የክልሉና የፌደራል ተቋማት የተካተቱ ሲሆን፥ ከ20 በላይ አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ ለመስጠት ያስችላል።
በተስፋዬ ኃይሉ